መንገዱ በፍጥነት ተጠናቆ ለትራንስፖርት አገልግሎት በመብቃቱም ህብረተሰቡ ደስታውን ገልጿል።
የአንበሳ ከተማ አውቶቢስ አገልግሎት ድርጅት እና ሸገር ብዙሃን ትራንስፖርት ከአራት ኪሎ በሽሮሜዳ ቁስቋም እንጦጦ ማርያም መድረሻውን ያደረገ አዲስ መስመር ከፍተው አገልግሎት መስጠት ጀመረዋል።
አዲሱ መስመር 10 ነጥብ 3 ኪሎሜትር ገደማ ሲሆን ተመጣጣኝ ታሪፍም ወጥቶለታል። አውቶቢሶቹ መደበኛ የትራንስፖርት አገልግሎት እየሰጡ ነው። የህብረተሰቡን የረጅም ጊዜ ጥያቄም በሚገባ መመለስ አሰችሏል።
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼