በኮንስትራክሽን ዘርፍ ፈጣኑን ቴክኖሎጂ እየተገበረ ያለው የልደታና ቂርቆስ ቤት ፕሮጀክቶች
የኩምካንግ አልሙኒየም ፎርሞርክ ቴክኖሎጂ (KumKnang Aluminum formwork technology) በመባል የሚታወቀውን የተለመደውን የኮንስትራክሽን ሂደት እጅግ ባሳጠረ መንገድ የሚተገበር ድንቅ ቴክሎኖጂ ተጠቅሟል፡፡
የደቡብ ኮርያ ቴክኖሎጂ ሲሆን በአሁን ሰአት በአለም ላይ ተመራጭ የቤት ልማት አይነተኛ አማራጭ ሆኗል፡፡
ልስን ቁርቋሮ ማፅዳት ትራንስፖርት የሚባሉ ጣጣዎችን በሙሉ በማስቀረት በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ አንድ ግድግዳ እስከ ወለሉ ድረስ በ7 ቀን ውስጥ ተሰርቶ የሚያልቅበት ዘመኑን የዋጀ ቴክኖሎጂ ነው፡፡
በኦቪድ ቴክኖሎጂ ግሩፕ( ovid group ) የሚገነባው ይህ ህንፃ በከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ መሰረት ድንጋይ ከተጣለ አሁን አንድ ወር የሆነው ሲሆን በአሁን ሰአት በአካባቢው በአንድ ወር ውስጥ ከአንድ ወር በፊት የተጀመረው ህንፃ በአሁን ሰአት በአካባቢው በአንድ ወር ውስጥ ጎልቶ መታየት የቻለ ህንፃ ሆኗል፡፡
ይህ ለከተማችን ለውጥ እና የከተማችንን የቤት ችግር በመሰረቱ በመፍታት ትልቅ ሚና የሚጫወት ነው፡፡