የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በዘንድሮ ክረምት በጎርፍ አደጋ ስጋት ያለባቸው አካባቢ የሚገኙ ነዋሪዎች ከወዲሁ አስፈላጊውን ሁሉ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ጥሪ ያቀርባል
አዲስ አበባ ከተማችን ከፈጣን ልማቷ፤ ከዘላቂ የዕድገትና የከተማ ማስዋብ እንቅስቃሴዎቾ በተጓዳኝ ለልዩ ልዩ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ስጋት የተጋለጠች ከተማ እንደመሆንዋ፤ አስፈላጊው ሁሉ ቅድመ ጥንቃቄ የወቅቶች መለዋወጥና የአየር ንብረት መዛባትን ተከትለው የሚከሰቱ አደጋዎችን ለመቀልበስ በተቀናጀ መልኩ መደረግ አለበት ብሎ ቢሮው ያምናል የድርሻውንም ኃላፊነት ከሚመለከታቸው ሁሉ ጋር እንደሚወጣ ከወዲሁ ለማሳወቅ ይወዳል ።
በለፉት ዓመታት ጐርፍ” የመሬት መንሸራተት”የቆሻሻ መደርመስና መሰል አደጋዎች በከተማችን ማጋጠማቸውን ተከትሎ የከፋ ሰብአዊና ቁሳዊ ጉዳት መድረሱ የሚታወስ ነው ፡፡ ሁላችሁም የከተማችን ነዋሪዎች እንደምታስታውሱት ባሳለፍነው ዓመት የክረምት ወራት በከተማችን የወንዝ ዳርቻዎች፣ በተዳፋት ቦታዎች፣ በረባዳማ አካባቢዎች የሚኖሩ ዜጎች የጎርፍ አደጋና የመሬት መንሸራተት ከፍተኛ ስጋት ያለባቸው በመሆኑ ከተማ አስተዳደሩ አስፈላጊውን ሁሉ ቅድመ ጥንቃቄ የአካባቢው ነዋሪዎችና የሚመለከታቸው አካላት በጣምራ እንዲያርጉ ሲያሳስብ መቆየቱ ይታወቃል ፡፡
ካለፉ ግዚያት ልምድ በመውሰድ ከተማ አስተዳደሩ ከፊታችን ባለው የክረምት ወቅት መሠል አደጋ በሰው ህይወትና ንብረት ላይ እንዳያጋጥም አስቀድሞ ለመከላከል እንዲቻል ከሚመለከታቸው ተቋማት የባለሙያዎች ቡድን በማዋቀር የጎርፍ አደጋ ስጋት ያለባቸውን አካባቢዎች የመለየት ሥራ በስፋት አከናውኗል ። በሁሉም ክ/ከተሞችና ወረዳዎች በባለሙያዎች በተደረገ የጥናት ውጤት መሰረት 161 አካባቢዎች በተለያየ ደረጃ የሚገለፅ የአደጋ ስጋት ያለባቸው ሲሆኑ ከእነዚህም መካከል ደግሞ 61 አካባቢዎች ከፍተኛ የጎርፍ አደጋ ስጋት ያለባቸው እና ተጋላጭ አካባቢዎች መሆናቸው በተደረገው ጥናት ተለይቷል ። በጥናቱ ምክረ ሃሳብ መሰረት ከተማ አስተዳደሩ አስፈላጊውን የሰው ኃይልና በጀት በመደብ ስጋቱን ለማቃለል የሚረዱ የቅድመ ጥንቃቄ ተግባራትን አስቀድሞ ማከናወን ጀምሯል።
ከተማ አስተዳደሩ በልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ህይወትና ንብረት ልከሰት የሚችልን የትኛውንም ድንገተኛ አደጋ ታሳቢ በማድረግ ፣ብሎም ስጋት አለባቸው ተብለው በተለዩ አካባቢዎች በሚገኙ ልዩ ልዩ ተቋማትና በልማት አውታሮች ላይ ጉዳት እንዳያጋጥም ኢንዲሁም በልዩ ልዩ አደጋዎች ምክንያት በአጠቃላይ በሀገራችን ኢኮኖሚ ላይ ልደርስ የሚችልን ጉዳት ታሳቢ በማድረግ የሚመለከታቸውን ተቋማት በማስተባበር አስቀድሞ በተደረገው ጥናት የተሰጡ ምክረ ሃሳቦችን ዋቢ በማድረግ በአስተማማኝ ሁኔታ ስጋቶችን ለመቅረፍ እንዲቻል በርካታ ተግባራት በሚከተሉት አካባቢዎች በስፋት እየተተገበሩ ይገኛሉ ።ለአብነት ያክል :-
በወንዝ ዳርቻ /አቅራቢያ/ የሚኖሩ የሕብረተሰብ ክፍሎችን የማንሳት እንቅስቃሴ “
በወንዞች ዳርቻ የአፈር መንሸራተትና የጎርፍ አደጋን ለመከላከል የሚያስችሉ ግንባታዎችን የማከናወን ሥራ”
በወንዞች ውስጥ የተጣሉ ቀሻሻዎችን በማንሳት የማጽዳት እንቅስቃሴ “
የወንዝ ዳርቻዎችን በአገር በቀል እጽዋት የመሸፈንና ፍሳሽ ማስወገጃ ቱቦዎችን የማፀዳት እንቅስቃሴ “
የወንዝ ዳርቻዎችን ወሰን ማስከበርና የአደጋ ስጋትን ለመቀነስ የሚያስችሉ በርካታ የቅድመ መከላከል ተግባራት በቅንጅት እየተከናወኑ መሆናቸውን ከተማ አስተዳደሩ ለማሳወቅ ይወዳል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮምዮኒኬሽን ቢሮ!