የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ እንዳስታወቁት ሀገራችን በአሁኑ ወቅት ያጋጠማትን ፈተናም ሆነ የኮረና ቫይረስ ወረርሽኝ ስጋትን ተቋቁመን በተሰራው ስራ በትምህርቱ ዘርፍ አበረታች ውጤት ተመዝግቧል ለዚህ ውጤት መገኘትም የመምህራን እና ባለድርሻ አካላት ሚናው ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ያጋጠማትን ችግሮች ተቋቁማ ወደ መደበኛ የልማት ስራዋ እንድትመለስ የትምህርት ሴክተሩ በተለይ መምህራን የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት በአግባቡ ሊወጣ እንደሚገባ ኃላፊው ጠቁመዋል ።
የትምህርቱ ማህበረሰብ የመጪው የ2014 የትምህርት ዘመን ከመደበኛ የመማር ማስተማር ስራን ከመስራት ባሻገር በሀገራዊ ጉዳዮች የበኩሉን አስተዋጽኦ ማበርከት የሚችልበትን ሁኔታ የሚያሳይ የመወያያ ርዕስ የቀረበ ሲሆን የውይይቱ ተሳታፊዎችም ለጀግናው መከላከያ ሰራዊታችን ደም ደም ለግሰዋል።