የከተማዋ የመንግስት እና የግል ትምህርት ቤት መምህራን ላለፉት 3 ቀናት ሲያካሂዱት የነበረው ውይይት የማጠቃለያ መርሀ ግብር  ተካሂዷል።
በአዲስ አበባ ከተማ “ትምህርት ቤት ለመማር፤ መምህራን ለማስተማር” በሚል መሪ ሐሳብ በተካሄደው ውይይቱ ላይ መምህራን ጠንካራ ጎኖች፣ ክፍተቶች፣ ጥያቄዎቻቸውን እና አስተያየቶቻቸውን አቅርበው ተወያይተናል።
የትውልድ ግንባታ መሰረት የሆኑት መምህራን በተለየ መልኩ የመኖሪያ ቤት እና የጥቅማ ጥቅም ጥያቄዎችን በየፈርጁ እየታየ በቅደም ተከተል እንደምንመልስ እንዲሁም የመደራጀትና ቁጠባ የመጀመር አስፈላጊነት ላይ ተግባብተናል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ