ልበ-ቀና ባለሀብቶችንና ሕዝባችንን በማስተባበር የበርካታ ነዋሪዎቻችንን ችግር መቅረፍ የሚያስችል የቤት እድሳት መርሀ-ግብራችንን የጀመርነው በልደታ ክፍለ ከተማ በተለምዶ ቆርቆሮ ሰፈር ተብሎ በሚጠራው ከ18 ዓመታት በላይ በቆርቆሮ ቤት ውስጥ የሚኖሩ 134 አባወራዎችን እና በአራዳ ክፍለ ከተማ ራስ መኮንን ድልድይ አካባቢ የሚኖሩ 15 አባወራዎችን መኖሪያ ቤት ዕድሳት በማስጀምር ነው፡፡
የከተማችንን ገጽታ የሚቀይር ታላላቅ ፕሮጀክቶችን ከመገንባት ጎን ለጎን በሰው ተኮር ስራዎቻችን የሀገር ባለውለታዎችንና አቅመ ደካማ ነዋሪዎችን ከከተማዋ ዕድገት ፍትሐዊ ተጠቃሚ እንዲሆኑ በትጋት መስራታችንን እንቀጥላለን::
ከንቲባ አዳነች አቤቤ