መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ሰራተኞች የፊታችን ሰኞ ሐምሌ 10 ከማለዳው 12:00 ሰዓት ጀምሮ በየአካባቢያቸው ችግኝ እንዲተክሉ ጥሪ እናቀርባለን::
በተለይም የመንግስት ሰራተኞች በእለቱ ስራ ስለማይኖር ከጠዋቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ የተመደባችሁበት የችግኝ መትከያ ቦታዎች ላይ በመገኘት አሻራችሁን እንድታኖሩ እናሳስባለን::
በእለቱ እስከ አንድ ሚሊዮን የሚደርሱ የከተማችን ነዋሪዎች በችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ ላይ ይሳተፋሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን እያንዳንዱ ነዋሪ በትንሹ አስር ችግኞችን የሚተክሉ ይሆናል::
በመሆኑም መላው የከተማችን ነዋሪ በየክፍለ ከተማውና በየወረዳው በተዘጋጁት የችግኝ መትከያ ቦታዎች ላይ በመገኘት ዛሬም እንደ ትናንቱ ሀገር ወዳድነቱን ችግኞችን በመትከል እንዲያረጋግጥ ጥሪያችንን እናስተላለፋለን፡፡