ይህንን ተከትሎም የቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በልዩ ሁኔታ የሚሰራቸውን ሰው ተኮር ተግባራት ክብር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በተገኙበት ይፋ አድርጎ ወደስራ ገብቷል፡፡
በትናንትናው ዕለትም ለዚህ ፕሮጀክት ማሳኪያ የሚሆኑ የቦታ መረጣ ያለበትን ሁኔታ ከንቲባዋ ተዟዙረው የጎበኙ ሲሆን ሁሉም ተግባራት በተያዘላቸው የጊዜ ገደብ በፍጥነት እየተከናወኑ መሆኑን ማረጋገጣቸውን ተናግረዋል፡፡
በቀጣይ ለቤት ግንባታ፣ለሸገር ዳቦ ፋብሪካና ማከፋፈያ፣ ለከተማ ግብርና፣ለምገባ ማዕከላት እና ለሌሎች ተግባራት የተለዩ ቦታዎች የግንባታ ዲዛይናቸው በአብዛኛው የተጠናቀቀ በመሆኑ ወደ ግንባታ ስራ እንዲገቡም ክብርት ከንቲባዋ አቅጣጫ አሰቀምጠዋል፡፡