
ከ57 አመት በላይ ያሰቆጠረው የመዘጋጃ ቤት ህንፃ፤ የቀድሞ ታሪካዊ ቅርፅን ሳይቀይር በ2.2 ቢሊዮን ብር የእድሳት ግንባታ ስራው ዘመናዊ ሆኖ ተጠናቆ ለምርቃት በቅቷል፡፡ይህ ታሪካዊና የከተማዋ ምልክት የሆነው የህንፃ እድሳት የከተማዋ የዘመናት ጉዞ አሻራ የያዘ ታላቅ ቅርስ ጭምር የሆነው ህንፃው ከተማዋ አለም ከደረሰበት የከተሞች እድገትና ውበትን በማላበስ ለተገልጋይ ምቹና አስፈላጊ አገልግሎቶችን ሁሉ ባሟላ መንገድ ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ተደራሽ እንዲሆንና አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ እንዲሆን ተደርጐ በከፍተኛ ጥረት እድሳቱ ተጠናቋል።