የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እያካሄደ ላለው የዝቅተኛ ማህበረሰብ የቤት እድሳት ፕሮግራም ሊሆን የሚችል 26ሺህ 890 የቤት ክዳን ቆርቆሮና ከ3500 በላይ ኩንታል ሲሚንቶ በድምሩ ከ14.5 ሚሊዬን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ በዛሬው እለት የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ደበሌ ቃበቶ ለከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ አስረክበዋል፡፡
በርክክብ ስነስርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት ከንቲባ ወሮ አዳነች ፕሮጀክቶቻችን ባቀድነው መሰረት እንዳሄድ እንቅፋት ሆኖብን የነበረው ችግር ግብዓቶቹ መንግስት ቤትም ባሉ ከመንግስት ቤት ውጪ ባሉ በህገወጦች እየተያዙ የፈለግነውን ያህል እንዳንሰራ እንቅፋት ሲሆንብን ቆይቷል ብለዋል፡፡
ጉምሩክ ኮሚሽን ከህገወጦች ጋር አንገት ላንገት ተናንቀው፤ ዛሬ ለህዝብ ጥቅም እንዲውል በማድረጋቸው ሊመሰገኑ እንደሚገባቸው አንስተዋል፡፡ እንደዚህ የሚሰሩ የሚያስተባብሩ ብዙ ተቋማት ብዙ መሪዎችና ብዙ ሰራተኞች ያስፈልጉናል ያሉት ከንቲባዋ ሌሎች የፌደራል ተቋማትም ከጉምሩክ ኮሚሽን ትምህርት መውሰድ አለባቸው ሲሉም አሳስበዋል፡፡
የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ደበሌ ቃበታ በበኩላቸው ኮሚሽኑ እነዚህን ንብረቶች ከተለያዩ የሃገሪቱ አካባቢዎች ራቅ ካሉ የጉምሩክ ጣቢያዎችና የኮንትሮባንድ ቁጥጥር ቦታዎች በማሰባሰብ ማምጣት መቻላቸውን ገልፀው አስተዳደሩ በተለይም ከንቲባ አዳነች አቤቤ ቀን ከለሊት በመስራት የህዝቡን ህይወት ለመቀየር የሚያደርጉትን ጥረት በእጅጉ እንደሚያደንቁና የአስተዳደሩ ጥረትን ለመደገፍ ኮሚሽኑ ምንጊዜም ከአስተዳደሩና ከህዝቡ ጎን እንደሚቆሙና ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል፡፡
አቶ ዘመኑ ደሳለኝ የቂርቆስ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ እንዲሁ በሰጡት አስተያየት የፌደራል ጉምሩክ ኮሚሽን መቀመጫው በክ/ከተማው ውስጥ በመሆኑ በቤት እድሳት እየተሳተፈ መሆኑን ገልፀው ህግን በማስከበር ከሚያገኙትም ውጤት የዜጎችን ኑሮ ለማሻሻል የሚያደርጉትን ጥረት የሚያስመሰግን መሆኑን ገልፀዋል፡፡
አቶ ዘመኑ ደሳለኝ የቂርቆስ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ እንዲሁ በሰጡት አስተያየት የፌደራል ጉምሩክ ኮሚሽን መቀመጫው በክ/ከተማው ውስጥ በመሆኑ በቤት እድሳት እየተሳተፈ መሆኑን ገልፀው ህግን በማስከበር ከሚያገኙትም ውጤት የዜጎችን ኑሮ ለማሻሻል የሚያደርጉትን ጥረት የሚያስመሰግን መሆኑን ገልፀዋል፡፡
የጉምሩክ ኮሚሽን ባለፈው ሳምንት በተመሳሳይ 15 ሚሊየን ብር የሚገመት ድጋፍ ማድረጉ የሚታወስ ነው፡፡