“ከጦርነት ወደ ብልፅግና በሰላም ጎዳና” በሚል መሪ ቃል በወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ በመላው በአዲስአበባ ወይይት እየተካሄደ ይገኛል ። የመንግስትና የግል የሚዲያ አመራሮች ፤ የጥበብ ባለሙያዎችና ታዋቂ ግለሰቦች የተገኙበትን የዉይይት መድረክ የመሩት የአዲስአበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ
አሁን ላይ በአሸባሪው ቡድን የተቃጣብንን ወረራ ለመቀልበስ በሁሉም መስክ የፈጠርነውን ሀገራዊ ህብረ-ብሔራዊ አንድነት ለዘላቂ ሰላምና ለሃገር ግንባታ ልንጠቀምበት ይገባል ብለዋል ። በመድረኩ ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥና በሃገር ሁለንተናዊ ልማትና ብልፅግና መረጋገጥ ላይ የሁሉም ህብረተሰብ ክፍል ፣ የሚዲያና የኪነ- ጥበብ ባለሙያዉ ሙያዊ ኃላፊነት ትልቅ ነዉ ያሉ ሲሆን ተሳታፊዎች ለዘመናት ሲንከባለሉ የቆዩ ችግሮችን ሁሉን አካታች በሆነ ብሔራዊ የዉይይት መድረክ ለመፍታት እንዲሁም በወራሪው ቡድን የወደሙ አካባቢዎችንና መሰረተ ልማቶችን መልሶ በማቋቋምና በወራሪው ቡድን የተያዙ ቀሪ አካባቢዎችን ነፃ በማድረግ ረገድ የሚጠበቁ ሚናዎች ላይ በመወያየት የጋራ መግባባት ላይ ደርሰዋል ። ክብርት ከንቲባ አያይዘዉም የተጎዳዉን ኢኮኖሚ በመገንባትና የብልፅግና ግባችንን በማሳካት በኩል የታየዉን ከፍተኛ ህብረ ብሔራዊ መነሳሳትና አንድነት አሟጦ መጠቀም ከሁላችንም ይጠበቃልም ነዉ ያሉት።
መሰል ዉይይቶች በመላው ከተማችን በሁሉም ህብረተሰብ ክፍል የሚካሄዱ ይሆናል።