እየተካሄደ ባለው የአዲስ አበባ ከተማ አዲስ የምክር ቤት ምስረታ ስነ-ስርአት ላይ በቀጣይ አምስት ዓመታት ምክር ቤቱን በአፈጉባዔነት እንዲመሩ በቀረበው እጩ መሰረት የተከበሩ ወ/ሮ ቡዜና አልከድር በአፈጉባዔነት በሙሉ ድምጽ ተመርጠዋል ።
ለህገ መንግስቱ ታማኝ በመሆን የመረጣቸውን ህዝብ በቅንነት እና በታማኝነት ስራቸውን በህግና በመሰረት ለመፈጸም ቃለ መሃላ ፈጽመዋል።
በተጨማሪም ፈይዛ መሀመድ በምክትል አፈጉባኤነት ተመርጠዋል ።