የፕሮጀክቱ አካል የሆነ እና ለትራፊክ ፍሰት እንዲሁም ለሰላም እና ጸጥታ ስራ የሚያግዙ 17 ፓትሮል ተሸከርካሪዎችን ለከተማ አስተዳደሩ አስረክበዋል፡፡በኢትዮጰያ የአለም ባንክ የኦፕሬሽን ማኔጀር ሚስስ ዳይና ፐትሪስኩ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የማዘጋጃ ቤታዊ ዘርፍ ስራ አስኪያጅ ለአቶ ጥራቱ በየነ ተሸከርካሪዎቹን አስረክበዋል፡፡በመርሃ ግብሩ በኢትዮጰያ የአለም ባንክ የኦፕሬሽን ማኔጀር ሚስስ ዳይና ፐትሪስኩ እንደገለጹት በአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት ዘርፉን ለማዘመን እና የመንገድ ደህንነትን ለማሻሻል አለም ባንክ የ200 ሚሊዮን ዶላር ፕሮጀክት ነድፎ እየሰራ ነው ብለዋል፡፡

ዛሬ ርክክብ የተደረገባቸው 17 ፓትሮል ተሸከርካሪዎችን የፕሮጀክቱ አንዱ አካል መሆናቸውን ሚስስ ዳይና ገልጸዋል፡፡በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የማዘጋጃ ቤታዊ ዘርፍ ስራ አስኪያጅ ለአቶ ጥራቱ በየነ በበኩላቸው የዓለም ባንክ ባለፉት ዓመታት በንጹህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት፣በትምህርት፣በጤና እና በምግብ ዋስትና ልማታዊ ሴፍቲኔት መርሃግብሮች በርካታ ድጋፎችን በማድረግ ላይ ይገኛል ብለዋል፡፡ባንኩ ዛሬ ያደረገው የተሽከርካሪ ድጋፍም የከተማዋን የትራፊክ ፍሰትን ለማሳለጥ እንዲሁም የሰላም እና ጸጥታ ስራን በይበልጥ ለማረጋገጥ እንደሚያግዙ አቶ ጥራቱ ጠቁመዋል፡፡