በኮልፌ ቀራንዩ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 እና 5 ተገኝተን የጎበኘን ሲሆን፣ በማዕከሎቹ የቴክኖሎጂ ስራዎች፣ የአገልግሎት አከባቢን ምቹ የማድረግ፣ የነዋሪ መረጃ አያያዝ ስርዓት በቴክኖሎጂ በመደገፍ የማደራጀት እንዲሁም ሌሎች አገልግሎትን የሚያቀላጥፉ ስራዎች ተሰርተዋል።
የዲጂታል አገልግሎት ከተጀመረባቸው የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት በተጨማሪ የመሬት፣ የገቢዎች፣ የግንባታ ፍቃድ፣ የንግድና የጤና ዘርፎች ላይ ቀልጣፋ አገልግሎት እየሰጠን ሲሆን ነዋሪዎቻችንን የሚመጥን ቀልጣፋ እና ዘመናዊ አገልግሎት ለመስጠት የጀመርናቸውን ስራዎች አጠናክረን እንቀጥላለን።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ