ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን ዓመታዊ እንቅስቃሴ ያስጀመሩት ከአራት ዓመታት በፊት የጠቅላይ ሚኒስትርነት ኃላፊነትን በተቀበሉበት የመጀመሪያ ዓመት ሲሆን፣ አላማውም የአረጋውያን፣ የአቅመ ደካሞች፣ የአካል ጉዳተኞች እና በኢኮኖሚ የተቸገሩ የህብረተሰብ ክፍሎችን መኖሪያ ቤት ለማደስ ነው። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ፣ በየዓመቱ ክረምት ከመግባቱ በፊት የቤት እድሳት መርሃ ግብር ሲከናወን ቆይቷል። በዚህ አመት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ‘የመደመር መንገድ’ ከተሰኘው መጽሃፋቸው ሽያጭ በተገኘ ገንዘብ በአዋሬ አካባቢ ተለይተው ለታወቁ 23 ግለሰቦች የመኖሪያ ቤት ግንባታ የሚደረግበትን ሂደት አስጀምረዋል: