ዛሬ በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ያስገነባነውን ባለ 8 ወለል ስማርት የወረዳ ማዕከልን እና የምስራቅ ፖሊ ቴክኒክ ሙያ ኮሌጅ ህንፃን መርቀን ለአገልግሎት ክፍት አድርገናል።
ማዕክሉ የኢንፎርሜሽን ቴክሎጂ መሰረት ልማት የተዘረጋለት፣ ለሰራተኞች እና ለተገልጋዮች ምቹ ሲሆን፣ አገልግሎት አሰጣጡን ዲጂታላይዝ በማድረግ ቀልጣፋ ፣ፈጣን እና ተደራሽ ለማድረግ ያግዛል።በያዝነው በጀት አመት ተጨማሪ 11 ስማርት የወረዳ ማዕከላት ግንባታ ስራም እናስጀምራለን።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ