በከተማችን የሰው ተኮር የልማት ስራዎች ዙርያ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ለለለያዩ በጎ ፍቃደኞች ባቀረብነው ግብዣ መሰረት በቀን እስከ 1 ሚሊዬን ዳቦ ማምረት የሚችል የዳቦ ፋብሪካ ከበጎ ፍቃደኛ የግል ባለሃብት ሂማ ማኑፋክቸሪንግ ፒኤልሲ ጋር በትብብር ተገንብቶ ለምረቃ በቅቷል፡፡
ይህ የዳቦ ፋብሪካ በተመጣጣኝ ዋጋ ለህብረተሰቡ ዳቦ የሚያቀርብ፣ ምንም ገቢ ለሌላቸው በነፃ የሚያቀርብ፣ ለብዙ የአካባቢው ወጣቶች የስራ እድል የፈጠረ እና እርስ በእርስ የመረዳዳትና የመተሳሰብ ባህላችንን የሚያሳደግ ጭምር ነው።
ሰርተን የምንለወጥባት፤ ነግደን የምናተርፍባት ከተማችን አዲስ አበባን ከራሳችን አልፎ ሌሎችንም ወገኖቻችንን የምናስታውስበት ማህበራዊ ሃላፊነታችንን በመወጣት በኩል ተምሳሌታዊ የሚሆን ተግባር ነው::
የከተማችንን አብሮነትና ፍቅር፣ ተሳስቦ የመኖር እሴት በመጠበቅ አሁንም በጀመርነው የሌማት ትሩፋት እንቅስቃሴ የግል ሴክተሩ፣ ግለሰቦችና ድርጅቶች ተሳትፎ በማድረግ የነዋሪዎችን ገበታ ሙሉ እና የተመጣጠነ እንዲሁም ለጎረቤትና ለአካባቢ የሚተርፍ እንዲሆን የበኩላችንን ሁሉ እንድናበረክት ጥሪ አቀርባለሁ!!
ወ/ሮ መህቡባ ሰይድ የሂማ ማኑፋክቸሪንግ ፒ ኤል ሲ ስራ አስኪያጅ ማህበራዊ ሀላፊነታቸውን ለመወጣት ላሳዮት ሀገር ወዳድነትና በጎነት ልባዊ ምስጋናዬን ለማቅረብ እወዳለሁ!!
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን አብዝቶ ይባርክ!!”
ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ