ቤተ መጻህፍቱ አሁን በሚሰጠው አገልግሎት በአማካይ በቀን ከ15 ሺህ በላይ አንባቢዎችን የሚያስተናግድ ሲሆን ዛሬ ባስጀመርነው 80 ሺህ መፅሃፍት ዲጂታል የተደረገበት አገልግሎት ከእጥፍ በላይ አንባቢዎችን መድረስ ያስችለናል::
ትውልዱ የሚያነብበት ስፍራ በማጣቱ እንጂ ሁኔታዎች ከተመቻቹለት በንባብ ራሱን ለማነጽ የሚተጋ መሆኑን በማየታችን ፤ተጨማሪ አዳዲስ ቤተመጻህፍት በየክፍለከተሞቻችን እየገነባን የተጠናቀቁትንም በቁሳቁስ እንዲሟሉ በማድረግ አንባቢ እና ምክንያታዊ ትውልድ ማፍራታችንን እንቀጥላለን::
ከንቲባ አዳነች አቤቤ