ከዚህ ዓመት ጀምረን በሚቀጠሉት 3 ዓመታት ፥
❖ የወላጆች የምክር እና ሁለንተናዊ አገልግሎት ድጋፍ ስርአት መዘርጋት፣
❖ 1000 የህጻናት መዋያዎችን ማልማት፣
❖ 12000 የህጻናት መጫዎቻ ስፍራዎችን መገንባት፣
❖ 1095 የቅድም አንደኛ ደረጃ ትምሀርት ቤቶቻችንን ትራንስፎርም ማድረግ፣
❖ 101 የጤና ጣቢያዎችን ለቀዳማይ ልጅነት ልማት አገልግሎት ምቹ ማድረግ
❖ 5ዐዐዐ ለወላጆችና አሳዳጊዎች የምክር አገልግሎት የሚሰጡ ሰራተኞችን አሰልጥኖ ማሰማራት እና
❖ የሀገራችንን ብሎም የአፍሪካን የቀዳማይ ልጅነት ስራዎች በምርምር እና ስርጸት የሚደግፍ የልህቀት ማእከል መገንባትን የምናከናውን ይሆናል።
በዚህም መሰረት፤
ዛሬ ባስጀምርነው የቀዳማይ ልጅነት ንቅናቄ ሳምንት በሕጻናት እንክብካቤና አስተዳደግ ዙሪያ ያሰለጠናቸውን 2500 ባልሙያዎች መርቀን ወደ ስራ አስገብተናል። በዚህ አጋጣሚ በርካታ የከተማችን ወጣት ሴቶች የስራ እድል ተፈጥሮላቸዋል።
በተጨማሪም በክበበ ፀሐይ ያስገነባውን የሕፃናት ክሊኒክ እና በልደታ ክፍለ ከተማ የተገነባውን የሕፃናት ማቆያ ማዕከል መርቀን ሥራ አስጀምረናል።
ከለውጡ ወዲህ ሰው ተኮር ፖሊሲን በከተማችን በመተግበር በትውልድ ግንባታ ላይ ያተኮሩ ስራዎችን በመስራት ለትውልድ ግንባታ ትኩረት ሰጥተን እየሰራን የምንገኝ ሲሆን፣ ወደፊትም ስራችንን አጠናክረን የምንቀጥል ይሆናል።
ይህ ፕሮግራም የተሳካ እንዲሆን የከተማችንና የፌዴራል መስሪያ ቤቶች፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በተለይም ቢግ ዊን ፊላንትሮፒስ እና በርናርድ ቫን ሊር የተባሉ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ከፍተኛ የቴክኒክ እና የፋይናንስ ድጋፍ አድርገውልናል። ሁሉንም በራሴ እና በከተማ አስተዳደሩ ስም እጅጉን እያመሰገንኩ እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እወዳለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጲያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!