ባለሙያዎቹ ከተማችን እየገነባቻቸው ካሉ ታላላቅ ፕሮጀክቶች ውስጥ ከፊሎቹን ጎብኝተው በፈተና ውስጥም ቢሆን ህዝብን የሚጠቅሙ ስራዎች መስራታችንን አድንቀው በልካቸው ለህዝብ ግንዛቤ መፍጠር አለመቻላችንን ነግረውናል፡፡
ባለሙያቹ ያሉባቸውን ጥያቄዎች እና ድጋፍ የሚሹባቸውን ጉዳዮች የጠቆሙን ሲሆን አንዳንዶቹን ከሚመለከታቸው ጋር በመነጋገር እንደምንፈታቸው ተግባብተናል፡፡
ኪነ-ጥበብ ትውልድ የሚያንጽ አብሮ የመኖር ዕሴቶቻችንን የሚገነባ በመሆኑ ከለውጡ ወዲህ በርካታ አንፊ ቴአትር ማሳያ ቦታዎችን ገንብተናል ፤ የአዳዲስ ቴአትር ቤቶች ግንባታንም ጀምረናል ፤ ነባሮቹን የማደስ እና አቅማቸውን የማጎልበት ስራ በመስራት ላይ እንገኛለን::
ቴአትር ቤቶችን ከመገንባት ባሻገር ታሪካዊ ማንነታቸው ተጠብቆ በአሰራርና በአደረጃጀት ባለሙያው ነጻነቱ ተከብሮ በሙያው እንዲጠቀም ማድረግ የሚያስችሉ ውሳኔዎችን በመወሰን ለባለሙያው እና ለጥበብ ድጋፍ ማድረጋችንን እንቀጥላለን::
ከንቲባ አዳነች አቤቤ