በለሚ ኩራ ከክፍለከተማ እስከ ወረዳ በ90 ቀን እቅድ ዉስጥ ዋና ዋና ተባለዉ የተለዩ ችግሮችን ለመፍታት ያለዉን አሰራር ፣ የአግልግሎት አሰጣጡን ምቹ ለማድረግና ለማዘመን የጀመርነው ስራ እንዲሁም ዝቅተኛ ገቢ ላላቸዉ የማህበረሰብ ክፍሎች የመኖሪያ ቤት ግንባታና የሌማት ትሩፋት ትግበራ በአንድ ወር ውስጥ እጅግ አበረታች በሆነ መልኩ እየተከናወነ መሆኑን ዛሬ በቦታው ተገኝተን ተመልክተናል ።
የአዲስአበባ ጥቃቅንና የሙያ ኮሌጆች ፣ በግል ተነሳሽነት ፣በበጎ ፍቃደኝነት በመሳተፍ ከጎናችን ሆናችሁ እየሰራቹት ባለው መልካም ስራ በእራሴና በከተማ ነዋሪው ስም ከልብ አመሰግናለሁ።
ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ