የታዋቂዋና አንጋፋዋ የሶማሊኛ ሙዚቃ ተጫዋች አርቲስት ሐዋ ታለን ቤት በመንግስትና በበጎ አድራጊ ግለሰቦች ድጋፍ እንደገና ተሰርቶ ዛሬ ተረክባለች።
የአርቲስት ሐዋ ታለን ቤት በአዲስ አበባ ከ/አስ/ር ባህል፣ኪነጥበብና ቱሪዝም ቢሮ በባህልና ስፖርት ሚኒስቴር እና ባለድርሻ አካላት ትብብር ተሰርቶ አልቆ ሙሉ እቃው የተሟልቶ እንድትረከብ ተደርጓል።
በዛሬው ዝግጅት ላይ አቶ ቀጀላ መርዳሳ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር እና ዶ/ር ሂሩት ካሳው የአ/አ ከተማ አስተዳደር ባህል ፣ኪነጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ቤቱን መርቀው አስረክበዋል።
አርቲስት ሐዋ ታለን የመጀመሪያዋ የሶማሊኛ ባህል ሙዚቃ ተጫዋች ስትሆን በሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት ለረጅም ጊዜ ስታገለግል ቆይታለች።
አርቲስቷ በተለይም ኪሪያ በተሰኘው ሙዚቃ በእጅጉ ትታወቃለች። ይህች የሀገር ባለውለታ የምትኖርበት ቤት ብዙ ችግር ያለበት በመሆኑ እንደገና ፈርሶ በአዲስ መልክ የተሰራውን ቤት ዛሬ ስትረከብ በጣም ደስተኛ መሆኗን ገልጻ መንግስትንና ጠቅላላ ድጋፍ ያደረጉ ልበ-ቅኖችን አመስግናለች።