የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ14ቱ ኮሌጆች በተለያየ የሙያ ዘርፍ ያሰለጠናቸው 10 ሺህ 120 ተማሪዎችን አስመረቀ ::
የዕለቱ የክብር እንግዳ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ባደረጉት ንግግር በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ስልጥነው ለተመረቁት ለሃገራችሁ መፃኢ እድል ተስፋ ልትሆኗት ለዛሬው ቀን በቅታችኋል እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል፡፡
ፈተና ሰብሮ እስካላስቀረ ድረስ ይቀርፃል ፤ ይሞርዳል በፈታኝ ሁኔታ የማለፍ ጥበብን ያስተምራል፥ ያሉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ የዛሬ ተመሪቂዎች በፈተና ሳትረቱ ለሃገራቸሁ ጠንክራችሁ መሰራት ይጠበቅባችኋል ብለዋል።
የህዝባችንን ተጠቃሚነትና የሃገራችንን ብልፅግና ለማረጋገጥ የኢንዱስትሪ ፣ የፈጠራ ስራና ቴክኖሎጂን ማስፋፋት ቁልፍ መሳርያ በመሆኑ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑንም ገልፀዋል::
የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት በሙያ፤ በክህሎትና በአስተሳሰብ የተሻሉ ሰልጣኞችን በማፍራት አገራችን በያዘችው ወሳኝ የለውጥ ምእራፍ የማይተካ ሚና የሚጫወቱ ናቸው፡፡
በከተማችን አዲስ አበባ የቴክኒክና ሙያ ተቋማትን በማጠናከርና በመደገፍ ለገበያው ብቁና ተወዳዳሪ የሰው ሃይል እንዲፈራ በዘርፉ ያለውን ገበያ ጉድለት እንዲሞሉ ክትትልና ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናግረዋል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በሥልጠና ጊዜ ቆይታቸሁ ያካበታችሁን ክህሎትና ስልጠና በአስተሳሰብ የተለወጣችሁ የሃገራችሁን ራዕይ ለማሳካት ውጤት ማፍራትን ግባቸሁ አድርጉ ሲሉ ተመራቂዎችን አሳሰበዋል ::
በአሁን ጊዜ በተለያዩ የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ከ40,095 በላይ ተማሪዎች በተለያየ የሙያ ዘርፍ እየሰለጠኑ መሆኑን ተገልጿል።
በምረቃ ስነስርዓቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ፣ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር መፈርያት ካሚል፥ የአ/አበባ ብልፅግና ፓርቲ ሃላፊ መለስ አለሙ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ በከር ሻልና ሌሎች የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።