የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉ ዛሬ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።
ሚኒስትሩ በመግለጫቸው፥ የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ በአዲስ አበባ እንዳይካሄድ ብዙ ቅስቀሳ እንደነበር አንስተው፥ ሆኖም አባል ሀገራቱ ለህብረቱ ህግና መርህ ተገዢ በመሆን ጉባኤው በአካል በአዲስ አበባ እንዲካሄድ መወሰናቸውን ነው ያመለከቱት።
በዚህም ውሳኔያቸው ለኢትዮጵያ ያላቸውን አጋርነት አሳይተዋል ያሉት ሚኒስትሩ፥ ይህም ተግባራቸው የሚያስመሰግናቸው ነው ብለዋል።
ሚኒስትሩ ባለፉት ሳምንታት ኢትዮጵያ ግዙፍና ታላላቅ ክብረ በዓላትን እና ሁነቶችን ሰላማዊ በሆነ መልኩ ማስተናገዷን አንስተዋል።
Source :- fana broadcasting