በአብሮነት የደመቀ የብዝሃ ቋንቋ፡ ሃይማኖት፥ በመተባበርርና መደጋጋፍ ውብ ልዩ ገፅታ ያላት አዲሰ አበባ ጥምቀትን ሃይማኖታዊ እሴቱንና ባህላዊ ትውፊቱን ጠብቆ በደመቀ ሁኔታ እንዲከበር ጉለሌ ክፍለ ከተማ እና ሸገር ከተማ አስተዳደር በጋራ እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል።
በውይይቱ ንግግር ያደረጉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ በአብሮነት የደመቀ የብዝሃ ቋንቋ፡ ሃይማኖት ባለቤት የሆነችው ከተማችን የአደባባይ በዓል የሆነውን የጥምቀት በዓል በአብሮነት እሴቱንና ባህላዊ ትውፈቱን ጠብቆ ማክበር ይገባል ብለዋል።
አዲስ አበባ ውስጥ ለመመሸገ የሚፈልገውን የፀረ ሠላም ሃይል ነዋሪው ክፍተት ስለማይሰጠው አላማውን ማሳካት አልቻለም ያሉት ከንቲባ አዳነች ልክ እንደ ትላንቱ ለሰላማች በጋራ እንቁም ሲሉም አሳስበዋል።
የጉለሌ ክ/ከተማ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ተስፋዬ ኦሜጋ በዓሉን በሰላምና በድምቀት ለማክበር ጉለሌ ክ / ከተማ እና ሸገር ከተማ አስተዳደር በጋራ እየሰራን ነው ብለዋል።
የውይይቱ ተሳታፊ የሆኑት የጉለሌ ክ/ከተማ እና የሸገር ከተማ አስተዳደር ነዋሪዎች ለሰላማችን ዘብ እኛው ነን የጥምቀት በዓልን በሰላም እንዳይከበር የተለያዩ የጥፋት ሴራ ለሚደግሱትም እድሉን አንሰጣቸውም ብለዋል።
ወጥቶ ለመግባት ሰላም ወሳኝ ነው ያሉት ተሳታፊዎቹ በመተባበርና መደጋገፍ ለከተማችን ብሎም ለሃገራችን ሠላምና ልማት አንድ ሆነን እንስራ ብለዋል የውይይቱ ተሳታፊዎች።
የአንድነታችን ሚስጥር በውይይት ችግሮቻችን መፍታት መቻላችን ነው ወጣቶችም የአባቶች ምክር ተቀብለን ለስላማችን ከፀጥታ አካላት ጋር እጅ ለእጅ ተያይዘን እንሰራለን ብለዋል።
የልማት ሥራዎች ፥ ሥራ እድል ፈጠራ፥ ሰላምንና ፀጥታን የተመለከቱ ጉዳዮች ከተሳታፊዎች ተነስተው ውይይት ተደረጉባቸዋል።