በቢሾፍቱ ከተማ የተከበረው የሆራ ሀርሰዴ ኢሬቻ በዓል ባማረ እና በደመቀ መልኩ ባህላዊ ሥርዓቱን ጠብቆ በሰላም መጠናቀቁን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።
የሰላም እና የፍቅር እንዲሁም የወንድማማችነት መገለጫ የሆነው የኢሬቻ በዓል ሥርዓቱን እና እሴቱን በጠበቀ መልኩ አጊጦ በሰላም እንዲከበር ሚናቸውን ለተወጡ የበዓሉ ታዳሚዎች፣ የፀጥታ ኃይሎች እና የአካባቢው ማኅበረሰብ ፖሊስ ምስጋናውን አቅርቧል።