በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በ2014 በጀት አመት በመንግስትና በህብረተሰብ ተሳትፎ የተሠሩ ፕሮጀክቶችና የልማት ስራዎች የምረቃ መርሀ ግብር በድምቀት ተከናውኗል።
ለህዝብ አገልግሎት እንዲሠጡ ታስበው 165,119,563ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነቡት እነዚህ የመንግስት ፕሮጀክቶች የአስፓልትና የኮብል እስቶን ንጣፍ፤ የቤተ-መፅሐፍት፤ ቦሪ 2ኛ ደረጃ ምድረ ግቢ፤ ቦሌ አዲስ G+4 የአስተዳደር ህንፃ ግንባታ ፤ መሪ 1ኛ ደረጃ ስፖርት ሜዳ እና ሌሎች ትላልቅ ፕሮጀክቶች እንደሆኑ በምረቃ ስነ-ስርአቱ ወቅት ተጠቅሷል።
በክብር እንግድነት በምረቃ ስነ-ስርአቱ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ አስፋው በመልዕክታቸው መዲናችንን የማስዋብ ጥረታችን ከሌሎች የልማት ጥረቶቻችን ጋር ጎን ለጎን ካስኬድነው በአጭር ጊዜ ውስጥ የ ከተማችንን ገፅታ መቀየር እንችላለን ሲሉም ተናግረዋል። አያይዘውም ፕሮጀክክቶቹ ለበርካታ ወጣቶች የስራ እድል የፈጠረ እና ለበርካታ ቤተሰቦችም መተዳደሪያ ሊሆን የቻለ ነው ብለዋል።
በፕሮጀክት ምርቃት ላይ የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ፕሮጀክቶቹ በተመረቁባቸው ወረዳዎች ነዋሪ ለሆኑት የማህበረሰብ ክፍሎች አስቀድመው የእንኳን ደስ አላቹ መልዕክታቸውን አስተላልፈው በተጨማሪም አክለው በክፍለ ከተማው የተገነቡት የመንግስትና የህብረተሰብ ተሳትፎ ፕሮጀክቶች የክፍለ ከተማውን ገፅታ ከመገንባት በዘለለ በትብብር ከሰራን ምን አይነት ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል ህያው ማሳያ ምስክር ነው ብለዋል።
በመጨረሻም በእነዚህ ፕሮጀክቶች ግባታ ወቅት አስተዋፅኦ ላደረጉ ግለሠቦች እና ተቋማት የእውቅናና የምስጋና ሰርተፍኬት ተበርክቷል