የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የዘጠና ቀናት እቅድ አፈፃፀም ተግባር ያለበትን ደረጃ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤ በተገኙበት ተገመገመ።
በዘጠና ቀናት ተግባራት ክፍለ ከተማውን ሞዴል ለማድረግ የሚያስችሉ በርካታ ስራዎች ለመስራት የታቀደ ሲሆን አነዚህንም ተግባራት ለማሳካት ትኩረት በመስጠት ወደ አፈፃፀም መገባቱም በውይይቱ ወቅት ተነስቷል።
ክፍለ ከተማው በዘጠና ቀናት በእቅድ ከያዛቸውና አመራሩንና ነዋሪውን አስተባብሮ ወደ ትግበራ ከገባባቸው ስራዎች መካከልም ከሌሎች ክፍለ ከተሞች የልምድ ልውውጥ በማድረግ ፣ አገልግሎትን በማዘመንና በማቀላጠፍ ፣ በፊት ሲነሱ የነበሩና የክፍለ ከተማውን ስም ሲያጠለሹ የነበሩ የአገልግሎት አሠጣጥ ክፍተቶችን በማረም ከፍተኛ ለውጦች እንዲመጡ ማድረግ መጀመሩ ፣ በቀን ውስጥከፍተኛ የተገልጋይ ቁጥር የሚያስተናግደው የመሬት አገልግሎትን ከወረቀት ንክኪ በፀዳ መልኩ ዲጂታላይዝ በማድረግ የሌብነትና ብልሹ አሠራሮች የመከላከል ብሎም ስርዓት ለማሰያዝ በጅምር ደረጃ ዲጂታላይዝ ለማድረግ መጀመር መቻሉ ፣የኑሮ ወድነትን መቅረፍ የሚቻልበት በክፍለ ከተማው ባሉት የእሁድ ገበያ መሸጫዎች የምርት አቅርቦትን በስፋትና በጥራት እንዲሁም በአነስተኛ ዋጋ እንዲቀርቡና አሁን ካለው በተጨማሪ የመገበያያ ቦታዎችን ለመጨመር እየተሠሩ ያሉ ስራዎች ተገምግሟል።
ከዚህ በተጨማሪም ሰው ተኮር የሆኑ አቅመ ደካሞችንና አረጋዊያንን ማዕከል ያደረገ የቤት ግንባታ ፕሮጄክቶች ፣ የመሰረተ ልማት ውሃ ፣ መብራት ፣መንገድ ፣ ዳቦ ፋብሪካ ግንባታ ና የመሸጫ ሱቆች ፣ የገብያ ማዕከል ና የከተማ ግብርናን ሞዴል ለማደረግ አየተሰራ መሆኑን ተገምግሟል ።