የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ለቢሾፍቱ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የ 1 ሚሊዮን 429,000 ብር የአይነት ድጋፍ አደረገ ፡፡
በድጋፍ ርክክቡ ላይ የክፍለ ከተማዉ ዋና ሥራ አስፈጻሚ እና የተለያዩ አመራሮች እንዲሁም የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አርሶ አደር ተወካዮች ተገኝተዋል ። የተደረገዉ ደጋፍ የእርድ ሰንጋዎችን ፤ የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን እና የምግብ ዘይትን ጨምሮ በአጠቃላይ ከ1.4 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለዉ የአይነት ድጋፍ ነዉ፡፡
በቀጣይም የክፍለ ከተማዉ አመራሮች የመከላከያ ሠራዊት የኢትዮጵያን ሉአላዊነትና የሕዝቦችን ሁለንተናዊ አንድነት ለማስጠበቅ የሚያደርጋቸውን ትግሎች በሁሉም ረገድ ከግንባር እስከ ደጀን እንደሚደግፉ ተናግረዋል ።
የመከላከያ ሠራዊቱን ወክለው ድጋፉን የተረከቡት ብርጋዴር ጀነራል ተገኝ ለታ የክፍለ ከተማው አስተዳደር በተከታታይ እያደረገ ላለው ድጋፍ አመስግነዋል ።