👉 የአዲስ አበባ ከተማ ከ85 በመቶ በላይ ውሃ የሚያገኘው ከፊንፊኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን እንደመሆኑ የጋራ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ይቻል ዘንድ በዚህ ሶስት አመት ውስጥ በልዩ ዞኑ የሚገኙ ወረዳዎች እና የገጠር ቀበሌዎች 30 መለስተኛ የውሃ ጉድጓዶች፣ 37 የመጸዳጃ ቤቶች እና 105 ኪ.ሚ ለህብረተሰቡ እና ለውሃ የሚሆን የመዳረሻ መንገድ ሰራዎች እየተሰሩ ይገኛል፡።
👉 በከተማ አስተዳደሩ 4.2 ቢሊዮን ብር በጀት የተሰራው ይህ ፕሮጀክት በቀን 86 ሺህ ሜትር ኪዩብ ውሃ ማምረት የሚችል ነው፡
👉 16 ጥልቅ ጉድጓዶች፣ እያንዳንዳቸው ከ2000 እስከ 5000 ሜትር ኪዩብ ውሃ የመያዝ አቅም ያላቸው 10 የውሃ ማጠራቀሚያ ጋን ግንባታን የያዘ ነው
👉 የ12 ኪሎ ሜትር ዋና የውሃ መሰመር፣ 72 ኪሎ ሜትር የውሃ ማሰባሰቢያ መስመር፣ 99 ኪሎ ሜትር የስርጭት መስመር ዝርጋታ፣ ሁለት ግዙፍ የግፊት መስጫ ጣቢያዎች እና 38 ኪሎ ሜትር የመዳረሻ መንገድን፣ እንዲሁም የኤሌክትሮ ሜካኒካል ስራዎች እና በጉድጓዶቹ አከባቢ የሚሰሩ የሲቪል ስራዎችን የሚያካት ነው።
👉 ይህም ፕሮጀክት የከተማ አስተዳደሩን ውሃ በቀን የማምረት አቅሙን ከ674ሺህ ወደ 760ሺህ ከፍ ያደርገዋል፡፡