የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ መለሰ ዓለሙ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ተገኝተው የሌማት ትሩፋት መርሐ ግብርን በይፋ አስጀመሩ
የሌማት ትሩፋት የተለየ ትኩረት የተሰጠው ከነፃነትና ከሉዓላዊነታችን ጋር ጥብቅ ቁርኝት ስላለው ነው ብለዋል አቶ መለሰ መርሐ ግብሩን ባስጀመሩበት ወቅት
ኢትዮጵያ በዚህን ሰዓት የኢኮኖሚ ነፃነቷን በቁርጠኛ ልጆቿ እያረጋገጠች ትገኛለች ለዚህ ትልቁ ማሳያዋ ስንዴን ወደ ውጭ ለመላክ መዘጋጀቷ ነው ብለዋል አቶ መለሰ
የሌማት ትሩፋታችን ሁሉንም ምግቦች ይዞ ከበለፀገ በአዕምሮና በአካል ብቁ የሆነ ዜጋን መፍጠር እንችላለን ያሉት አቶ መለሰ ባለፈው ዓመት የሰራነውን የከተማ ግብርና ስራ እንደ አቅም ተጠቅመን በዚህ ዓመትም የሌማት ትሩፋታችንን በማበርከት ህዝባችንን ተጠቃሚ እናደርጋለን ብለዋል።
የቂርቆስ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶክተር ብሩክ በበኩላቸው በምግብ እራስን መቻል ከሀገር ሉዓላዊነት ጋር ጥብቅ ቁርኝት እንዳለው ጠቅሰው ሌማታችን እንዲሞላ ለሌማት የሚሆን ግብዓት ከጓሯችን ማምረት ያስፈልገናል ብለዋል
የሌማት ትሩፋት ከማስጀመር ባለፈ ግለሰቦች በአስተሳሰብ ደረጃ ተቀብለው ወደ ራስ መቻል እንዲገቡም በትኩረት እንሰራለን ። ለሌሎች አርአያ እንዲሆኑም እንደግፋለን ብለዋል ዶክተር ብሩክ
በዕለቱም በከተማ ግብርና ስራ ውጤታማ የሆኑ ግለሰቦች ተሞክሯቸውን አቅርበው ሌሎችም የነሱን ፈለግ እንዲከተሉ ጥሪያቸውን አቅርበዋል