ተሳታፊዎቹም በኢትዮጲያ የማንደራደር፤ ሰላም ወዳደድ ህዝቦች ስለሆንን ከሌሎች ወንድም ህዝቦች ጋር በመሆን የሚጠበቅብንን ለመወጣት ዝግጁነታቸውን አረጋግጠዋል።
መድረኩን የመሩት የክ/ከተማው ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ሙሉእመቤት ታደሰ እንደተናገሩት የትግራይ ህዝብ ከሌሎች ወንድም ህዝቦች ጋር ሆኖ ለሀገር እድገት፣ ለሰላምና ለሁለንተናዊ የሀገር ግንባታ የበኩሉን አስተዋፆ ሲያደርግ የነበረ ህዝብ ነው፤ ወደ ፊትም የራሱን አሻራ እያሳረፈ ኢትዮጲያን በማሻገር ሂደት የድርሻውን እየተወጣ ይቀጥላልም ሲሉ ገልፀዋል።
ወ/ሮ ሙሉእመቤት አክለውም የትግራይ ህዝብ ጥንትም ሆነ ዘሬ በኢትዮጲያዊነት የማይደራደር፣ ሰላምና ፍትህን የሚሻ ህዝብ ነው፤ አሁን ያለው ለውጥ እንዲመጣም የራሱን በጎ አሻራ አሳርፏል፤ ይህንን ሰላም ወዳድ የሆነ ህዝብ ከህወሓት ነጥሎ ማየትም ያስፈልጋል ብለው አሁን ላይ በሽብር ቡድኑ ምክንያት በትግራይና በሌሎች ህዝቦች ላይ እየደረሰ ያለው መከራና ስቃይ በቶሎ እንዲያበቃ መንግስትን ማገዝና መደገፍ ይገባል ሲሉ ገልፀዋል።
የትግራይ ተወላጆች በበኩላቸው በመድረኩ አጥፊውን ከሰላማዊ ዜጎች መለየት ያስፈልጋል፤ እኛ የትግራይ ህዝቦች በኢትዮጲያ የማንደራደር፤ ሰላም ወዳደድ ህዝቦች ስለሆን ከሌሎች ህዝቦች ጋር ሁነን ቡድኑን እንታገላለን ፤የከተማዋን ብሎም የአገሪቷን ሰላም ለማረጋገጥም ከመንግስት ጎን በመሆን የሚጠበቅባቸውን እንደሚወጡም አረጋግጠዋል።