የዘንድሮው የመስቀል በዓል በከፍተኛ ድምቀት ብሎም ነባር ሃይማኖታዊ እሴቱንና ትውፊቱን ጠብቆ እንዲከበር የከተማ አስተዳደሩ ከአራዳ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች ጋር ዛሬ የምክክር መድረክ ተከናውኗል።
በምክክር መድረኩ የተገኙት የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ አት ጃንጥራር አባይ በዓሉ ሀይማኖታዊ እሴቱን ጠብቆ እንዲከበር ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።
የመስቀል በዓል በዩኔስኮ በማይዳሰሱ ቅርስነት የተመዘገበ ነው ያሉት አቶ ጃንጥራር፣ የአደባባይ በዓሉ ያለ ምንም የፀጥታ ችግር እንዲከበር የከተማዋ ነዋሪዎች የተለመደውን ትብብር እንዲያደርጉ አሳስበዋል።
ሰሞኑን በከተማችን አንዳንድ የሚታዩ የፀጥታ ስጋት ምልክቶች ስላሉ፣ ህብረተሰቡ ከምንጊዜውም በላይ አካባቢውን በመቃኘት አጠራጣሪ ሁኔታዎችን ሲመለከት ለፀጥታ አካላት እንዲጠቁሙም አሳሰበዋል።