የአዲስ አበባ ከተማ ደረቅ ቆሻሻ አስተዳደር ኤጀንሲ ከቂርቆስ ክፍለ ከተማ ጋር በመቀናጀት
በተካሄደው የፅዳት ንቅናቄ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች፣በጎ ፍቃደኛ ወጣቶች ፣የፅዳት አምባሳደሮች ፣ ታዋቂ አርቲስቶችና አትሌቶች እንዲሁም ልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል፡፡
በነገው ዕለትም ከተለያዩ የእምነት ተቋማት የተውጣጡ የሀይማኖት አባቶች፣ የአዲስ አበባ ሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ አባላት እና ተወካዮች ፣የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ የአዲስ አበባ ሀገረስብከት አድባራት እና ገዳማት አስተባባሪዎች፣በጎፈቃደኛ ወጣቶች እና ነዋሪዎች የደመራ በዓል የሚከበርበትን መስቀል አደባባይ እና አካባቢውን የማስዳት እና የማሳመር መርሃግብር ይካሄዳል፡