መላው የአዲስ አበባ ህዝብ ፣የእምነት አባቶቻችን ፣ ምእመናን ፣ወጣቶች፣ በየደረጃው የምትገኙ አመራሮች፣ የፀጥታ ሃይሎቻችን ፣የከተማችን የሰላም ሰራዊት አባላት እና የደንብ ማስከበር አገልግሎት ሌት ተቀን ከህዝባችን ጋር ተቀናጅታችሁና ተሳስራችሁ በመስራት ላሳያችሁት የላቀ ትጋት፣ ቁርጠኝነትና ላስገኛችሁት ውጤት ልባዊ ምስጋናዬን በከተማ አስተዳደሩና በከተማችን ህዝብ ስም ላቀርብላችሁ እወዳለሁ!!
አንድነታችን እና ህብረታችን መድመቂያ ጌጣችን ፣ በዓሎቻችን የአብሮነታችን መገለጫ ፤ የኢትዮጵያዊነታችን ሚስጥር ናቸው!!
ፈጣሪያችን ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን አብዝቶ ይባርክ!”
ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ