ውድድሩን አዲስ አበባ ከተማ በ46 ወርቅ ፣ በ30 ብር ፣ እና በ34 ነሀስ በአጠቃላይ 110 ሜዳሊያዎችን ሰብስቦ 1ኛውን ወጣቶች ኦሎምፒክ በበላይነት አጠናቋል::
ኦሮሚያ ክልል 27 የወርቅ ፣ ,24 የብርና ፣15 የነሀስ በድምሩ 66 ሜዳሊያዎችን ሰብስቦ ውድድሩን ሁለተኛ በመሆን አጠናቋል::
ደቡብ ክልል ደግሞ 9 የወርቅ ፣13 የብር ፣ 21 የነሀስ ሜዳሊያዎችን በድምሩ 43 ሜዳሊያዎችን በመሰብሰብ ውድድሩን በ3ኛነት ፈፅሟል::
የውድድሩ አጠቃላይ አሸናፊ አዲስ አበባ ከተማ ነገ ወደ አዲስ አበባ ሲገባ ደማቅ አቀባበል ይደረግለታል ተብሎ ይጠበቃል::