ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በኢትዮጵያ የመጀመሪያ እና ዘመናዊ የተባለውን እና በክብር ዶ/ር አበበች ጎበና ስም የተሰየመውን የእናቶች እና ህፃናት ሆስፒታል በይፋ አስመረቁ።ሆስፒታሉ በ700 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባ ሲሆን በውስጡ ከ400 በላይ አስተኝቶ መታከሚያ አልጋዎችን ያካተተ ሲሆን በተመሳሳይ ሰዓት ለሰባት እናቶች በቀዶ ጥገና የማዋል አገልግሎት ይሰጣል ።

በ22 ሺህ ካሬ መሬት ላይ ያረፈው ይህ ዘመናዊ የእናቶች እና ህጻናት ልዩ ሆስፒታል በተመሳሳይ ሰአት ሰባት እናቶችን በቀዶ ጥገና ማዋለድ ያስችላል። የከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ ለእናቶችና ህጻናት ጤና ቅድሚያ በመስጠት ለመለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ ታስቦ የተጀመረውን ህንፃ ግንባታውን በማሻሻል ወደ ሆስፒታልነት እንዲቀየር ተደርጓል።በሆስፒታሉ የምርቃት ስነ ስርአት ላይ የክብር ዶክተር አበበች ጎበና፣ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት መዓዛ አሸናፊ፣ የጤና ሚኒስትር ደኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ ፣የሃይማኖት አባቶችን ጨምሮ ታዋቂ እና ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል፡፡