“በእርግጥ የምናገለግለው ህዝብ ከልካችን በላይ የማይጠይቀን ፤ ስንሰራ ከአንጀቱ የሚመርቀን ፤ ስናለማ የሚያግዘን ፤ስናጎድል የሚገስፀን ፤ ላቅ ሲልም እንደ ወላጅ ሸንቆጥ የሚያደርገን ፤ ለስራ ስንነሳ አንጀቱን አስሮ ከጎናችን የሚቆም ፤ ሚዛናዊ የሆነ ፤ በፍትሃዊነት የሚዳኘን ፤የሚገባንን የሚሰጠን አስተዋይና ታላቅ ህዝብ ነው፡፡
ህዝባችንም ከመቼውም ጊዜ በላይ ከጎናችን እንደሚቆም እናምናለን!!
አደራችን ትልቅ ቢሆንም፣ ህዝባችንን አስተባብረን ፤ መክሊታችንን እያበዛን ፤ለላቀ ውጤት መትጋታችንን እንቀጥላለን!!”
ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ