የፌዴራል መንግሥት እና የህወሓት የሰላም ስምምነት ኮሚቴ አባላት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት ለመጀመሪያ ጊዜ በሐላላ ኬላ ተገናኝተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለመጀመያ ጊዜ ከሰላም ስምምነት ትግበራ አስተባባሪ ኮሚቴ ጋር ምክክር አደረገዋል።
በውይይታቸው እስካሁን በሰላም ስምምነቱ አፈፃፀም ዙሪያ የተከናወኑ ተግባራት የተገመገሙ ሲሆን በቀጣይ ትኩረት በሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች ላይ አቅጣጫ ተቀምጧል።
የሰላም ድርድሩ ኮሚቴ አስተባባሪዎች ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የመጀመሪያውን የገፅ ለገፅ ግንኙነት ያደረጉት የገበታ ለሀገር ፕሮጀክት አካል በሆነው ሐላላ ኬላ ነው።