የሰላም፣ የፍቅር፣ የመከባበር፣ የመቻቻል ተምሳሌት የሆነው የፊቼ ጨምበላላ በዓል በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ ሁነቶች ተከብሯል።
የፊቼ ጨምበላላ በዓል ከዘመን መለወጫነቱ ባሻገር ከሰላም ተምሳሌትነቱ ከአቃፊነቱ አንጻር ለአንድነት የጎላ መሆኑ በበዓል አከባበር ዝግጁቱ ላይ ተገልጿል።
የፊቼ ጨምበላላ በዓል የሰው ልጅ ለአከባቢ ጥበቃ እና ለእንስሳት ልዩ ስፍራ የሚሰጥም ነው።
በበዓል አከባበር ስነ ስርዓቱ ላይ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳቦ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መለሰ ዓለሙ፣ በም/ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ጥራቱ በየነ፣ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች እና የሀገር ሽማግሌዎች ተገኝተዋል።