ሙዚየሙ ትላንት ብቻ ከ75 ሺህ በላይ ጎብኚዎችን አስተናግዷል
የሳይንስ ሙዚየም ጉብኝት ጊዜ ለአንድ ወር መራዘሙን ኢትዮ ቴሌኮም አስታወቀ።
የኩባንያው ዋና ስራ አስፈፃሚ ወይዘሪት ፍሬህይወት ታምሩ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንደገለፁት የሳይንስ ሙዚየሙን ለመጎብኘት ባለው ሰፊ ፍላጎት ምክንያት የመጎብኛ ጊዜውን መጨመር አስፈልጓል።
እንደ ወይዘሪት ፍሬህይወት ገለፃ፤ የሳይንስ ሙዚየሙ በ19 ቀናት ውስጥ 357ሺህ ጎብኚዎች የጎበኙት ሲሆን ባሳለፍነው ቅዳሜና እሁድ ብቻ 109ሺህ በላይ ሰዎች ጎብኝተውታል።
ዋና ስራ አስፈፃሚዋ መዚየሙን ከአዲስ አበባ ውጪ ያሉ ዜጎች እንዲጎበኙት ለማድረግ የሚያስችል ስራ እየተከናወነ መሆኑንም አስረድተዋል።
ሙዚየሙ ትላንት (ጥቅምት 13 ቀን 2015 ዓ.ም) ብቻ ከ75 ሺህ በላይ ጎብኚዎችን አስተናግዷል ብለዋል።