የአዲስ አበባ ከተማ ሴቶች ማኅበር 8ኛ መደበኛው ጉባዔውን በማካሄድ ላይ ይገኛል::
ጉባኤውን በንግግር የከፈቱት የማኅበሩ የቦርድ ሰብሳቢ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከለውጡ ወዲህ በሪፎርም ራሱን መልሶ ያደራጀው የሴቶች ማኅበር ከፖለቲካ ድርጅት ነጻ ሆኖ ለሴቶች ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ያደረጋቸው ትግሎች ውጤት ማሳየት መጀመራቸውን ገልጸዋል::
ማህበሩ ባደረገው ትግል የተገኙ ውጤቶች እንዲጠናክሩ ድክመቶች ተለይተው እንዲታረሙ ጉባዔው መክሮ አቅጣጫ እንደሚያስቀምጥ ይጠበቃል::