የከተማ አስተዳደሩ በሚያደርገው ድጎማና የግብዓት አቅርቦት በቀን 900 ሺህ ሲያመርት የነበረው አሁን 1.5 ሚሊየን ዳቦ ማምረቱ የዋጋ ንረትን በማረጋጋት የበኩሉን አስተዋፅኦ እንዲያበረክት ከስምምነት ላይ መደረሡን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ገለፁ።

ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ የሸገር ዳቦ ፋብሪካ የከተማችንን እና በዙሪያው የሚገኙ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን የሕብረተሰብ ክፍል የዳቦ ፈላጎት እንዲቀርፍ ታስቦ የተቋቋመ ቢሆንም ፋብሪካው በለፉት ጊዚያት በሙሉ አቅሙ ወደ ምርት ሂደት ባለመግባቱ የዳቦ እጥረትና የኑሮ ውድነት ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን የከተማችንን ነዋሪዎች በእጅጉ ተፈታትኗል ብለዋል።ፋብሪካውን ያጋጠመውን የስንዴ አቅርቦት ውስንነት በመፍታት በሙሉ አቅሙ ወደ ምርት ሂደት እንዲገባ ለማስቻል የከተማ አስተዳደሩ ትኩረት ሰጥቶ በመስራት ለፋብሪካው የስንዴና ልዩ ልዩ አስፈላጊ ድጋፎችን ሲያከናውን በቆየው መሠረት ከወትሮው በተሻለ ትኩረት ሰጥቶ ድጋፍ እያደረገ ይገኛል ።