የቀድሞ የሰራዊት አባላት የሀገር መከላከያ ሰራዊትን የሚደግፍ ፤አሸባሪው ህወኃትን የሚያወግዝ ሰልፍ በመስቀል አደባባይ አካሂደዋል፡፡
በመርሃ ግብሩ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የቀድሞ የሰራዊት አባላት ለኢትዮጵያ ዘብ ለመቆም ላሰዩት ተነሳሽነት ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ያሳዩት ቁርጠኝነና ተነሳሽነትም የህወሓት አሸባሪ ቡድን የሰራዊት አባላትን የአንድ የፖለቲካ ስርዓት አገልጋይ አድርጎ ሲፈርጅ መቆየቱ ምን ያክል ከእውነት የራቀ መሆኑን አመላካች ነው ብለዋል፡፡
የጁንታው የጥፋት ቡድን የትግራይ ህዝብንም ነው የበደለው፣ህዝቡን ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋር ለመነጠልም ብዙ ሰርቷል ብለዋል።
በዚህም ይህ አሸባሪ የጥፋት ቡድን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እንደቀበር ተባብረን እንስራ ስል መልዕክቴን የማስተላልፈው ለትግራይ ህዝብም ጭምር ነው ሲሉ ገልፀዋል፡፡
ኢትዮጵያ እበለፅጋለሁ ፣የህዳሴውን ግድብ ገንብቼ አጠናቅቃለሁ፣ህዝቦቼ እየለመኑ መኖር የለባቸውም ብላ እየሰራች ባለችበት ወቅት የኢትዮጵያን ተፈጥሮአዊ ሃብት መበዝበዝ የለመዱ፣ጫና ለመፍጠር የሚሞክሩና የኢትዮጵያን ትንሳዔ ለማደናቀፍ የሚሰሩ ሃይሎች መኖራቸውን ተናግረዋል፡፡
ሆኖም ኢትዮጵያን ከትንሳዔና ብልፅግና የሚያስቆም አንዳች ምድራዊ ሃይል የለም ብለዋል ።
በመርሐግብሩ የቀድሞ የሰራዊቱ ጀነራሎች መልዕክት አስተላልፈዋል ።