ከራሳቸው ሥራና ጥቅም ይልቅ የሀገርን ጥቅም ያስቀደሙት ዘማቾች እነሱ ባለመኖራቸው ሰብላቸው እንዳይበላሽና እንዳይከስም በመላ ሀገሪቱ የተለያዩ አካላትና ግለሰቦች ለዘማች ቤተሰቡ ድጋፍ እያደረጉ ይገኛሉ።
ከቂርቆስ ክፍለ ከተማ የተወጣጡ ሰራተኞችና አመራሮች በዛሬው ዕለት በሰበታ ከተማ የዘማች ቤተሰቦችን ሰብል በመሰብሰብ ድጋፍ አድርገዋል።
በመርኃግብሩ ላይ የተገኙት የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዘመን ደሳለኝ ሁሉም በሚችለው አቅም ከተጋገዘ ከአቅም በላይ የሚሆን አንዳችም ኃይል እንደሌለ ገልጸው በክፍለ ከተማው ለዘማች ቤተሰብ የሚያደርጉት ድጋፍ ወደፊቱም እንደሚቀጥል ተናግረዋል።
በሰብል ስብሰባው ላይ የተሳተፉት የክፍለ ከተማው አመራሮችና ሰራተኞች በበኩላቸው የሀገርን ልዑላዊነትና ሰላም ለማስከበር የዘመቱትን ዘማቾች የቤታቸው ሥራ እንዳይሰናከል ሁሉም ማኅበረሰብ ድጋፉን ማስቀጠል አለበት ብለዋል።