ሐምሌ 12/2014 በክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ የወንጀልና የትራፊክ አደጋ ምርመራ ዘርፍ ሀላፊ የሆነት ዋና ኢንስፔክተር ባህሩ ተክሌ በላኩትመረጃ እንዳስታወቁት ሀላፊው ጊዜያዊ ስልጣኑን በመጠቀም ሰነድ አልባ የሆነን መኖሪያ ቤት ህጋዊ ካርታ ሰጥሻለሁ በሚል የማጭበርበር ቃል ከአንዲት ግለሰብ አትላስ አካባቢ ከአንድ ግለሰብ ሱቅ በር ላይ ገንዘቡን ሲቀበል እጅ ከፍንጅ ተይዞ ጉዳዩ እየተጣራ ነው ብለዋል።
ዋና ኢንስፔክተሩ አያይዘውም ከጉዳዩ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ሌሎች ግለሰቦችን በማጣራት ላይ መሆኑን ገልፀው አገልግሎትን በገንዘብ ለመሸጥ የሚሞክሩ ሌሎች ግለሰቦችም ከዚህ በመማር ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አሳስበዋል።
ህብረተሰቡም ድርጊቱን በማጋለጥ ሂደት ላደረገው አስተዋጽኦ አመስግነው እንዲህ ዓይነት ሀላፊነት የጎደላቸው ግለሰቦችን ሲያገኝ በአፋጣኝ ለፖሊስ እንዲጠቁምም ጥሪያቸውን አቅርበዋል።