ገበያዎቹ ለማህበረሰቡ አማራጭ የመገበያያ ስፍራ ከመሆን ባሻገር የግብርና፣ የኢንዱስትሪና የፋብሪካ ምርቶችን በቀጥታ ለሸማቹ በማቅረብ ለምርቶች ዋጋ መረጋጋት ብሎም የኑሮ ውድነትን ለመቅረፍ ትልቅ አስተዋፅዖ በማበርከር ላይ ይገኛሉ::
በአሁኑ ሰዓት 172 የቅዳሜና እሁድ የገበያ ቦታዎች በከተማችን የሚገኙ ሲሆን በሁሉም ቦታዎች ምርቶች ከመደበኛው ገበያ ዝቅ ባለ እና ተመጣጣኝ በሆነ ዋጋ ለህብረተሰቡ በመቅረብ ላይ ይገኛሉ::