አዲስ አበባ፣ ግንቦት 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቆየውን የሃይማኖቶች መቻቻልና መከባበር አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር እድሪስ ገለጹ፡፡
ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር እድሪስ እንደገለጹት÷ በእስልምና እና ክርስትና ሃይማኖቶች መካከል ያለው አንድነትና መከባበር በቀጣይም በተጠናከረ መንገድ ሊቀጥል ይገባል ሲሉ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡
በሃይማኖት ተከታዮቹ መካከል እውነተኛ መተሳሰብ ሊኖር እንደሚገባ ገልጸው÷ ወጣቶች የሃይማኖት አባቶችን ምክር በመስማት ራሳቸውን ከጥፋት መጠበቅ እንዳለባቸውም አሳስበዋል፡፡
የየትኛውም ሃይማኖት ተቋማት የአክራሪዎች መደበቂያ መሆን እንደሌለባቸው እና መንግስትም ሕግ የማስከበር ስራውን በትኩረት መከወን እንዳለበት ተናግረዋል፡፡
በምናለ አየነው