1. የዘርፉ የስምሪት መስመሮች በከተማዋ ዳርቻዎችና አዋሳኝ አካባቢዎች፣ በሰፋፊ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ሳይቶች እና በተለዩ አንዳንድ የከተማው የውስጥ ለውስጥ አጫጭር መንገዶች ላይ የተወሰነ ይሆናል
2. በዚህ ስምሪት ስርዓት ውስጥ መሳተፍ የሚችሉት ኮድ 1 ሰሌዳ ያላቸው ባለሦስት እና ባለአራት እግር በተለምዶ ባጃጅ ተብለው የሚጠሩ ተሸከርካሪዎች ብቻ ይሆናሉ
3. በቢሮው በተለዩ የስምሪት መስመሮች ብቻ አገልግሎት ይሰጣል
4. የመጫን አቅም 3 ሰው ብቻ ይሆናል
5. ለየትኛውም ርቀት ታሪፍ 5 ብር ነው
6. መደበኛ የትራንስፖርት አገልግሎት መስጫ ሰዓት ከጠዋቱ 12፡00 ጀምሮ እስከ ምሽቱ 03፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ነው
7. በዋና መንገድና አደባባይ ላይ የስምሪት መነሻና አገልግሎት አሰጣጥ አይፈቀድም፣የነዳጅ ድጎማ አይደረገም