የብልጽግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ በዛሬው ዕለት ያጠናቀቀውን መደበኛ ስብሰባ ተከትሎ አባላቱ የአረንጓዴ አሻራ ካኖሩ በኋላ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እየተካሄደ ያለውን የአድዋ 00 ኪሎሜትር ፕሮጀክት ጎብኝተዋል።
የማዕከላዊ ኮሚቴው አባላት በአዲስ አበባ አራዳ ክፍለ ከተማ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸውን የፍራፍሬ ችግኞች በመትከል በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ተሳትፎ አድርገዋል።
በመቀጠልም በግንባታ ላይ ያለውን የአድዋ 00 ኪሎሜትር ፕሮጀክት ተዘዋውረው የጎበኙ ሲሆን በጉብኝቱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ስለ ፕሮጀክቱ ዓላማ፣ ይዘትና ፋይዳ እንዲሁም አሁን ስላለበት ደረጃ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
የብልጽግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ በሀገራዊ የሰላምና ደህንነት፣ የልማትና የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ጉዳዮች ላይ ለሁለት ቀናት በጥልቀት ከተወያየ በኋላ የተለያዩ አቅጣጫዎችን በማሳለፍ ውይይቱን አጠናቋል።
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ፤